የካይዘን ፍልስፍናን ለኢንደስትሪ መር ኢኮኖሚ ግንባታ የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ::

በድሬደዋ ካይዘን ኢንስቲትውዊትና በድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ የመጀመሪያው የካይዘን ትግበራ ፎረም ተካሂዷል።

ከኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ ጋር ግንኙነት ያላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

መድረኩን የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዲ ሙክታር ኢንዱስትሪን በሚፈለገው ልክ በጥራትና በምርታማነት ለማስቀጠል ባለ ድርሻ አካላት ተቀናጅቶ መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

ከባለድርሻ አካላቶች መካከል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ ሲሆን የተማረ የሰው ሀይል በማፍራት ብሎማ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችሉ ጠቁመዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር የካይዘን ፍልስስናን በመተህበር እንዲሁም ሌሎች ሪፎርሞችን በመተግበር አሁን ላይ የማምረት አቅምን ከነበረበት 44 ፐርሰንት ወደ 54 ፐርሰንት ማሸጋገር መቻሉን አቶ አብዲ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም መሻገር የሚገባን ብርካታ ችግሮች መኖራቸውን ችግሮችን በመለየትና የጋራ መፍትሔ ማበጀት እንደሚያስፈልግ ቸብራርተዋል።

ከምርትና ምርታማነት፣ ከምርት ጥራትና ከማምረት አቅም አንጻር የተፈለገውን ውጤት ለማግኘትና የታለመውን ግብ ዕውን ለማድረግ ከካይዘን ፍልስፍና ጋር የተግባር የሠው ሀይል እንደሚያስፈልግም ነው አቶ አብዲ የጠቀሱት።

ምክትል የቢሮ ሀላፊው አክለውም ያልተመጣጠነ ማክሮ ኢኮኖሚን የተመጣጠነ ለማድረግ ካይዘን መር ፍልስፍናና አሰራር መተግበር ያስፈልጋል ብለው ኢንደስትሪን ከደገፍን የበለጸገች ሀገር በመፍጠሩ ሂደት የድርሻችንን አበረከትን ማለት ነው ብለዋል።

በአስተዳደሩ ከምርት ብክነት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በተደረገው ጥረት 53% መድረሱን በመድረኩ የተጠቀሰ ሲሆን የውጭ ገቢ ምርቶችን በመቀነስ ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የምርት ጥራት ማሻሻያ ላይ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ገደፋዬ በበኩላቸው የሀገር ኢኮኖሚን በተሻለና በተስተካከለ ቁመና ላይ ለማቆም የካይዘን ትግበራ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነት እንዳለባቸው ነው የተናገሩት።

የአስተዳደሩ ከይዘን ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ግዛው እንደገለፁት በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሎም በአፍሪካ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎችን ለመፍጠር በጥራት ምርት ማሻሻያ ላይ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በቀጣይ የአገልግሎት ተቋማትንና አምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ መደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ሀገራችን በአለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ድርጅት አባል ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ በኢኮኖሚው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በምርት ጥራትና ማሻሻያ(ከይዘን)ላይ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አቶ አብዲ ሙክታር ገልፀዋል።

በመጨረሻም የካይዘን ፍልስፍና ዙሪያ በቀረቡ ሶስት ሠነዶች ላይ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል። በመድረኩም ለተሞክሮ የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በካይዘን ኢንስቲትዩት እና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የፎቶ ኢግዚቢሽን በካይዘን ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችም ለታዳሚው ቀርበው አውደ ጥናቱ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *