ከድሬዳዋ የልማት ግስጋሴ ጎን ለጎን የከተማዋን ፅዳትና ውበት አስጠብቆ መጓዝ እንደሚገባ ተገለፀ::
የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም ድሬዳዋን ንፁህ፣ ፅዱና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ ዘርፎች አበረታች የልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተናግረው፤ በአጠቃላይ የከተማዋን የልማት ግስጋሴ በሚመጥን መልኩ የከተማ…


