#DGC ታህሳስ 13/2017
በድሬዳዋ አስተዳደር በድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ለድሬዳዋ ህዝብና ለአካባቢው አጎራባች ክልሎች የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት ዶ/ር አቤል መልካሙ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ በህይወት እያሉ ለሰሩት ዘመን ተሻጋሪ ስራ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በስሙ ጤና ጣቢያ የመሰየም ተግባር እውን ሆኖ በበፊት ስሙ ገንደቆሬ ጤና ጣቢያ ተብሎ የሚጠራው ማዕከል የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በዶ/ር አቤል መልካሙ ስም በመሰየም ዶ/ር አቤል መልካሙ መታሰቢ ጤና ጣቢያን ይፉ የማድረግ እና በስሙ ለሚቋቋመው ፋዉንዴሽን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ተካሂዷል ።
በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ዶ/ር አቤል በህይወት እያለ የሰራውን መልካም ስራ ሊያስቀጥል የሚችልና ግብ ማድረስ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዉ ፋዉንዴሽኑ ላይም የአስተዳደሩ ድጋፍ እንደማይለይ ገልፀዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ፅጌሬዳ ክፍሌ በበኩላቸው ዶ/ር አቤል ይደግፋቸውና ይረዳቸዉ የነበሩ ማህበረሰቦች በሙሉ ድጋፋቸዉ እንዳይቋረጥ ዋነኛ የፋውንዴሽኑ መመስረት አላማ መሆኑን ገልፀዋል ።
የዶ/ር አቤል መልካሙ ቤተሰቦች በስሙ ለተደረገዉና ለሚደረጉ ነገሮች በሙሉ አስተዳደሩና በዚህ ተግባር የተሳተፉትን በሙሉ አመስግነዋል ።
Dire tv


