የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም ድሬዳዋን ንፁህ፣ ፅዱና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ ዘርፎች አበረታች የልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተናግረው፤ በአጠቃላይ የከተማዋን የልማት ግስጋሴ በሚመጥን መልኩ የከተማ ፅዳትና ውበት ላይ ተተኩሮ መሰራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ በበኩላቸው የዛሬው የውይይት መድረክ በዋነኝነት አመራሩን ለቀጣይ ተልኮ ለማዘጋጀት እንዲሁም በአስተዳደሩ እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ክፍተት የታዩባቸው ቦታዎች ላይ አተኩሮ ለመስራት መሆኑን ጠቁመዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:- አገኘሁ ሸዋረጋ


