በአስተዳደሩ የሚገኙ ወጣት ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ሊተገበር ነው

#DGC ታህሳስ 15/2017

ፒትኮ (petco) ኢትዮጵያ ከ CAWEE እና ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ዲቨሎፕመንት ጋር በመተባበር enabiling young women and men to find dignified and fulfillig jobs (EYWM) በሚል ፕሮጀክት ወጣት ሴቶች በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ውስጥ በስፋት ተቀጥረው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሆኔታ የሚፈጥር ፕሮጀክት በድሬዳዋ አስተዳደር ሊተገብር ነው።

በዚህም ፕሮጀክቱን በድሬዳዋ አስተዳደር ለመተግበር በዛሬው እለት ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ጋር ውይይት ተደርጓል።

ክቡር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ድሬዳዋ የንግድና የኢንደስትሪ ማእከል መሆኗን በመግለፅ ፕሮጀክቱ ወጣቶችን ተጠቃሚና የስራ ባለቤት እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ድሬዳዋ ላይ መተግበሩም ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ከንቲባ ሀርቢ በማብራራት ለፕሮጀክቱ መሳካት የሚጠበቅብንን ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።

የፔትኮ ኢትዮጵያ ሲኒየር ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር አየለ ሄገና ፕሮጀክቱ በቀጣይ አምስት አመታት በተለዩ ሴክተሮች ላይ ወጣቶችን ለማብቃት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የፔትኮ ኢትዮጲያውያን ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ወ/ሮ ምህረት ተክለማሪያም በበኩላቸው ፕሮጀክቱ 80/100 የሚሆኑ ሴት ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረው ፕሮጀክቱ ለድሬዳዋ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለውም ጠቁመዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:- ቴድሮስ ልዑልሰገድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *