የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በከተማው ከሚገኙ ባሀለብት አቶ ሰኢዶ ሀሰን ጋር በመተባበር በበጎ ፍቃድ የአረጋውያን ቤት እድሳት ያስገነባውን ቤት አጠናቆ በዛሬው እለት ለባለቤቶቹ አስረክቧል::
በዚህም በርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን በመገኘት ለባለቤቶቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ፤ አቅመ ደካማ ወገኖችን በርብርብ ማገዝ ከፍተኛ የሆነ የህሊና እርካታ እንዳለው ገልፀዋል። አቶ ገበየሁ አያይዘውም ቤቱ በጥራትና በፍጥነት ታድሶ መጠናቀቁን ጠቁመው ሁሉም የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህልን ማዳበር ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ቤት የተገነባላቸው አቅመ ደካማ ወገኖች በበኩላቸው…


