የከተማችን አሽከርካሪዎች አመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በአል ለማክበር ወደ ከተማችን ሚመጡ እንግዶች በጥሩ ስነምግባር እና በተቀመጠው ታሪፍ ብቻ ሊያገለግሉ እንደሚገባ ተጠቆመ።

በአስተዳደሩ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የመንገድ ደህነነት እና መድህን ፈንድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ይህነኑ ለመቆጣጠር በሙሉ አቅሙ ባለሙያዎቹን አሰማርቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ኢንጅነር ሁሴን ጀማል በከተማ መውጫ ደንገጎ መስመር እንደሁም ትናንት ማምሻ በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ጣቢያ የድሬደዋ ጣቢያ በመገኘት የታሪፍ ቁጥጥር ሂደቱን ተመልክተዋል።

ከመልካጀብዱ ፖሊስ ጣቢያ ጋር በመቀናጀት በጣቢያው ለሚገኙ የታክሲ ማህበር አባላት ግንዛቤ መፈጠሩን የገለፁት ኢንጅነር ሁሴን ከግንዛቤው ባሻገር የድሬደዋን እንግዳ ተቀባይነት እሴት በሚጥሱት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል ለዚህም ከመልካ ጀብዱ ፖሊስ ጣቢያ እና ጣቢያው ከሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በዛሬውም እለት ይህንኑ በማጠናከር በድሬደዋ አለም አቀፍ ኤርፖርት ባለሙያውን በማሰማራት የታከሲ የታሪፍ ስርአት ክትትል ይደረጋል ነው ያሉት።

መረጃው የአስተዳደሩ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነቶ ክፍል ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *