በዚህም በርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን በመገኘት ለባለቤቶቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ፤ አቅመ ደካማ ወገኖችን በርብርብ ማገዝ ከፍተኛ የሆነ የህሊና እርካታ እንዳለው ገልፀዋል።
አቶ ገበየሁ አያይዘውም ቤቱ በጥራትና በፍጥነት ታድሶ መጠናቀቁን ጠቁመው ሁሉም የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህልን ማዳበር ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ቤት የተገነባላቸው አቅመ ደካማ ወገኖች በበኩላቸው ከዚህ ቀደም በፈራረሰና ዝናብ በሚያስገባ ቤት ውስጥ እየኖሩ ይቸገሩ እንደነበረ ጠቁመው፤ አሁን ላይ ቤታቸው በመታደሱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመርሀ-ግብሩ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስን ጨምሮ የአስቤዛ ድጋፍም ተበርክቷል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:- ሙሉዓለም ደሴ


