ከኢትዮ ጅቡቲ የድንበር ወሰን የተመለሱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አህመድ ቡህ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ከንቲባ አህመድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መጋቢት 17 /2012 ዓ.ም 814 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ከኢትዮ ጅቡቲ የድንበር ወሰን የተመለሱ ዜጎችን ድሬዳዋ መግቢያ ጫፍ 5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ ህንፃ ውስጥ ለ 14 ቀናት አስፈላጊው ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገላቸው በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ተመላሾች በሚኖራቸው ቆይታ ለበሽታው ተጋላጭ እንዳይሆኑ በየሁለት ሜትር ርቀት እንዲቆዩ መደረጉን…


