ህብረተሰቡን ያማከለ መሠረተ ልማት ለመዘርጋት ፍላጐትን አካቶ ማቀድ እንደሚገባ ተገለፀ

     

    ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም የካፒታል ኢንቨስትመንት እቅድን ለማካሄድ በአስተዳደሩ ባሉ ቀበሌዎች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሴቶችና ወንዶች  እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን አሳታፊ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተሠጥቷል፡፡

    የከተሞችን የመሠረተ ልማት የማስፋፋት አቅም ለማጠናከርና በከተሞች  መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሞች ተመርጠው የበጀት ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡

    በዚህ ድጋፍ አማካኝነትም ባለፉት ዓመታት በርካታ የመሠረተ ልማት ስራዎች በድሬደዋ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ ተሠርተዋል፡፡ ይህ ፕሮግራም በሚቀጥሉት ዓመታትም በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል እንደሆነና ካለፉት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ትምህርት በመውሰድ በጥራትና በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን በእቅድ ለመያዝና በቀጣይነት ለሚከናወኑ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራ ከምንጊዜም በበለጠ በተጠናከረ ቅንጅት፣ ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር ስራዎች እንደሚመራ አቶ ነጂብ ኢድሪ በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ አስታውቀዋል፡፡

     

    ወ/ሪት ትህትና በለጠ የካፒታል ኢንቨስትመንት የእቅድ ባለሞያ እንደተናገረችው የዚህ አይነት የውይይት መድረኮች ሲዘጋጁ የመጀመሪያ አለመሆኑንና ከዚህ ቀደም በተካሄዱት የእቅድ ውይይቶች ህብረተሰቡ በተለይም ሴቷ የምትፈልገው እንዲሠራላት በመጠየቋ በፍላጐት ላይ የተመሠረቱ የመሠረተ ልማት ስራዎች በመከናወናቸው አፈፃፀማቸውም በጥሩ መልኩ የሚገመገም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አሁንም መድረኩ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ውይይቱን ለሶስት ቀናት በማድረግ ሴቶችን ለብቻ ወንዶችንም ለብቻ በማወያየት አንዱን ቀን ደግሞ በጋራ በመምከር ውሳኔ ላይ የሚደረስበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

    በውይይቱ ላይ ተሣታፊ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት ሃሣብና አስተያየት የዚህ አይነቱ ተሞክሮ ወደፊትም ቢሆን ሊሰፋ እንደሚገባና የህዝብን ፍላጐት መሠረት ያደረገ እቅድ መታቀዱ ችግራችንን ፈቺ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ በተለይም ሴቷ በዚህ መሠረተ ልማት በብዙ መንገድ ተጠቃሚ መሆኗን ጠቁመዋል፡፡

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *