ድሬደዋ በፊት የነበራትን ስሟን ለመመለስ በአስተዳደሩ ተሾሚዋች የፅዳት ስራ በዘጠኙም ከትማ ቀበሌዋች ተካሄደ።

    ድሬዳዋን ከወንጀል እና ከቆሻሻ እናፅዳት”በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የፅዳት ስራ በየወሩ የሚካሂድ ሲሆን የአስተዳደሩ ተሾሚዋች በዘጠኙም የከተማ ቀበሌዋች ከጠዋቱ 12ሰዓት ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ ጠዋት አፅድተዋል።

    በ05 ቀበሌ የፅዳት ስራው ላይ ተሳታፊ የነበሩት በአስተዳደሩ በምክትል ከንቲባ መአረግ ከኒትባ መሀዲ ጊሪ የፀዳት ስራውን አስመልክተው እንደተናገሩ ከተማዋን ማፅዳት ብቻ ሳይሆን በውስጣችን ያለውን ቂም በቀል በማፅዳት ከተማዋን ወደ ነበረችበት ውብና አረንጓዴ እንዲሁም ሁሉም በፍቅርና በሰላም በመቻቻል የሚኖርባት ከተማ እንድትሆን ሁሉም ተግቶ መስራት አለበት ብለዋል። ከኒትባው ከዚህም ጋር በማያያዝ ድሬዳዋ ቀደም ባሉት አመታት የነበራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ ድሬዳዋ ፅዱና ውብ ከተማ ነበረች በማለት በአሁኑ ወቅት ግለኝነት ከመስመር እያውጣን በመሆኑ ኃላፊነትን የመንግስት ብቻ አድርጎ መመልከት ይስተዋላል ብለዋል። የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ከድር ጆሀር በ08 ቀበሌ በተካሄደው የፁዳት ስራ ላይ እንደተናገሩት አመራሩ የህብረተሰቡ አገልጋይ በመሆኑ ሰርቶ የማሰራት ግዴታ አለበት ።ይህም በመሆኑ ሰኔ15 እና 16/2011አመራሩ የፅዳት ስራ በከተማዋ አካሄዳዋል ብለዋል። ቀደም ባሉት ጊዜያት በከተማዋ በትራንስፖርት ችግር ቆሻሻ በወቅቱ ባለመወገዱ ቆሻሻው ከተማዋን ሲበክል እንደነበር በመግልፅ ይህንን ችግር ለመፍታት አስተዳደሩ 10 ገልባጭ መኪናዋችን ለመግዛት መወሰኑን ጠቁመዋል። ቀደም ባሉት አመታት የተለያዪ ስራዋችን ብንሰራም ቅንጅታዊ አሰራር ስለሚጎለው ዉጤታማ አልሆንም ያሉት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፋአድ ከድር በቀጣይ ጊዜያት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በስፋት መስጠት ይኖርብናል ብለዋል። በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ የፅጥታ አካላት በሰጡት አስተያየት የፅጥታ ሀይሉ የህብረተሰቡ አንዱ አካል በመሆኑ በዘመቻው በመሳተፍ አጋርነታችንን ማሳየት ይኖርብናል በማለት ከዚህም ጎን ለጎን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ወንጀልን የመከላከል ኃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል። ከጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላለፈውን መልዕክት በአስተዳደር ተግባራዊ ለማድረግ የችግኝ ተከላ በአስተዳደሩ አዲስ እየተገነባ ባለው ማረሚይ ምክትል ከንቲባና ታራሚዋች እንዲሁም የማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላቤቶች ተሳትፈዋል ። የፅዳት ስራው ወር በገባ በመጀመሪያው ቅዳሜ በየወሩ እንደሚካሄድ በምክትል ከንቲባው ተጠቁማል።

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *