ድሬዳዋ በፊት የነበራትን ስሟን ለመመለስ በነገው እለት የአስተዳደሩ ተሾሚዋች የፅዳት ዘመቻ ሊያካሂዱ ነው።

     “ድሬዳዋን ከወንጀል እና ከቆሻሻ እናፅዳት”በሚል መሪ ቃል ሴኔ15 እና16/2011 በአስተዳደሩ አመራሮችና

    የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ እንዲሁም የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በጋራ በመሆን በከተማዋ ክምር ቆሻሻ ባለበት አካባቢዋችና በየቤቱ ሳይወገዱ የቀሩ ቆሻሻዋችን የማፅዳት ስራ እንደሚከናወን የአስተዳደሩ ምክትል ከኒትባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ከድር ጆሀር ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል። ምክትል ከንቲባው ከዚህም ጋር በማያያዝ የከተማዋ ፅዳት በመጠበቅ በቅርቡ እንደ ሀገር የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ በአስተዳደሩ እንዳይስፋፋ አመራሩ የሚያገለግለውን ማህበረሰብ ጤና እንዲጠበቅ ሀላፊነቱን መውጣት እንዳለበት ገልፅዋል። የፅዳት ስራው በአስተዳደሩ አመራሮች በወየወሩ እንደሚካሄድ ገልፅዋል። ምክትል ከኒትባው ለህብረተሰቡ ባስተላለፉት መልእክት ህብረተስቡ ድሬደዋን ወደ ቀድሞ ስሟ ለመመለስ በሚሰራው የፅዳት ዘመቻ ከአመራሩ ጋር አጋርነቱን በማሳየት የባለቤትነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

    በትዕግስት ቶሎሳ

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *