በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ብቸኛ የሆነውና በቅርቡ አንደሚመረቅ እቅድ ለተያዘለት የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቁና ገበያው የሚፈልገውን ሰው ኃይል ለማሰልጠን የሚያስችል ስራ በመስራት ላይ እንዳለ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
በከተማዋ የሚገኘው የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅዋ በበኩሉ ያልታየና የጥናት ስራዬን አጠናቅቄ ወደ ትግበራ ገብቻለሁ ብሏል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከኒትባና የንግድ ኢኑዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጆሀር በፓናል ውይይቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የቴክኒክና ሙያ ዘርፎች በማህበረሰቡ ያለው አመለካከት ቀድሞ ከነበረው መሻሻልን እንዳሳየ በመጠቆም ዘርፉ ከተማዋ ላይ የተሻለ የስራ እድልን በመፍጠር ላይ መሆኑን ገለፀዋል፡፡
አቶ ከድር አያይዘውም በከተማዋ በፌደራል መንግስት ከፍተኛ ወጪ ተደርጎበት በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ለሚጠበቀው የኢንዱስትሪ ፓርክም ከሌሎች ከተሞች ተሞክሮን በመውሰድ በተለያዩ መስኮች ለስራ አጥ ወገኖች ሰልጣናን በመስጠት ለፓርኩ ለማቅረብ እየተሰራ እንዳለ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚከፍቱ ፋብሪካዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ በአዳዲስ የሙያ መስኮች የሰው ኃይልን ለማሰልጠን የሚያስችላቸውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡
ኮሌጅ ዲን ከዚህም ጋር አያይዘው የስራ አጥነት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ በተጠኑና ገበያው የሚፈልጋቸውን የሙያ መስኮች ላይ ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ ነን ብለዋል፡፡
በከተማዋ ያለው ማህበረሰብ ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለው አመለካከት የተሻለ እንዲሆን ኮሌጃቸው ሲምፓዚየሞችን በማዘጋጀት ታዳጊዎች ቅድመ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማስቻል ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
በድሬዳዋ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ወጣት ሲሳይ እና አበራ በሰጡት አስተያየት መንግስት በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ላይ በርካታ ክህሎት ያላቸውና ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀሩ የፈጠራ ስራ ባለቤቶች በቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡


