ህብረተሰቡ አካላዊ እንቅስቃሴን በማዘወተር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታ እንዲከላከሉ ጥሪ ቀረበ

    ለ4ኛ ጊዜ በአስተዳደራችን ድሬዳዋ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማህበረሰቡ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ፡፡

     

    የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል  ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሠኢድ ጨምሮ በርካታ ማህበረሰቦችና ከተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉበት በዚህ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ ላይ አቶ ዩሱፍ እንደተናገሩት ጤናማ ማህበረሰብ መፍጠር ብንችል ስለልማት ስለኢኮኖሚና  ስለፖለቲካ ማውራት እንችላለን ብለዋል ፡፡

    የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ወ/ሮ ስንታየሁ ደበሳ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ስነ-ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት ጥሪ ተደርጎላቸው በዚህ ተግባር የተሳተፉትን ሁሉ አመስግነው ቢሮው ሰዎች አካላዊ እንቅስቃሴን በማዘወተር በሽታን እንዲከላከሉና በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በየደረጃው ባለው የመንግስት ተቋማት እንዲሁም በቀበሌ እያከናወኑ ቢሆን የተሳታፊ ቁጥር ግን መሻሻል ያልታየበት እንደሆነ በመግለፅ በቀጣይ  ተስፋ ባለመቁረጥ በ5ኛው ዙር በርካታ የግንዛቤ ስራን መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

    በተያያዘ ዜና የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በተለያዩ የአሀገሪቱ ክልልሎች የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ በአስተዳደሩም አንድ ታማሚ በመገኘቱ እንዳይስፋፋ  ለሚዲያ ባለሙያዎች፣ ለትምህርት ቤቶች፣ ለቀበሌ ኮሙዩኒኬሽኖችና ለቀበሌ ማስተባበሪያዎች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ቀድመው ማህበረሰቡ ውስጥ በመግባት ግንዛቤ እንዲፈጥሩ ስለበሽታው ምንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰቷል፡፡

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *