ወጣቱ የአመለካከት ለውጥ በማምጣት የተሰጠውን ሀገራዊ ተልእኮ ለመወጣት የይቻላል መንፈስ እንዲኖረው ጥሪ ቀረበ፡፡

    የድሬዳዋ አስተዳደርና የሀረሪ ክልል ወጣቶችና እስፖርት ኮሙሽን  ከፌደራል ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ሚኒስተር  ጋር በመተባበር ለአስተዳደሩና  ለሀረሪ  ክልል ወጣቶች  የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡

     

         የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሙሽን ኮሙሽነር አና  ዑመር በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች የሚታየውን አንፃራዊ ሠላምና ለማስቀጠል  በመረጋጋትና ከስሜታዊነት በመፅዳት ምክናታዊ አስተሳሰብን በመያዝ የተሻለ ሀሳብን በመደገፍ የሀሳብ ልህቅናን የበላይነት የምታፀባሩቁበት ሁኔታ ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡

    ኮሙሽነር ከዚህም ጋር በማያያዝ ማንኛውንም አካል  ለሀገር ገፅታ ግንባታ  የድርሻውን በማድረጉ በርታ ቀጥል በማለት ለሀገር ፀር የሆኑ ለለውጥ እንቅፋት የሆኑ ቤሄርን ከቤሄር ሀይማኖትን ከሀይማኖት እንዲሁም ጎጠኝነትን አስተሳሰብን ወጣቱ  በገልፅ ለመተቸት ምክንያታዊ የሆነ ወጣት ለመፍጠር እንደዚህ አይነት መድረኮች በተደጋጋሚ ጊዜ መዘጋጀታቸው አስፋላጊ ነው ብለዋል፡፡

    ኮሙሽነር አክለውም ወጣቱ የሚሰጠውን ሀገራዊ ተልእኮ እኔ እችላለው በማለት የመፈትሄ አካል ነኝ የሚል አስተሳሰብ እንዲኖረው እንዲህ አይነት መድረኮች መዘጋጀታቸው  ወሳኝነት የጎላ ነው በማለት   የሀገር ግንባታና የወጣቶች  የእርስ በእርስ ልምድ ልውውጥ አንዲኖር እንዲሁም ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ለመቀየር ወደፊት የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ  ምን መሆን አለበት ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ስልጠና ነውም ብለዋል፡፡

    የድሬደዋ ወጣቶች እና ስፖርት ኮሙሽን የወጣቶች ማሳተፍና ማብቃት አብይ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ እስክንድር አህመድ በስልጠናው ላይ አንደተናገሩት አንፀራዊ  ሰላሙን ለማስቀጠል ኮሙሽኑ በ2012 በጀት  አመት በአመለካከት ለውጥ ላይ ተከታታይነት ያለው ስልጠና ለመስጠት እቅድ ማቀዱን በመግለፅ ይህም በመሆኑ ወጣቱ በራሱ የመወሰን ልምዱን ያዳብራል ብለዋል ፡፡

    የስራ ሂደቱ አክለውም ወጣቱ የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጣ  ከስልጠናው ጎን ለጎን በአስተዳደሩ  ባሉት ወጣት መአከላት በወር አንድ ጊዜ የራሳቸውን አጀንዳ በመቅረፅ ከአቻቸው ጋር የጋራ ውይይት በተጨማሪም በወር አንድ ጊዜ በሰላምና በአንድነታችን ዙሪያ የኪነ-ጥበብ መድረክ በማዘጋጀት ግንዛቤያቸውን እንዲያሰፉ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

    በፌደራል ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስተር የወጣቶች ንቅናቄና ተሳትፎ ዳሪክተር አቶ ማቲያስ አሰፋ ስልጠናውን አስመልክቶ እንደተናገሩት የተለወጠ ማንነት ያለው ወጣት ለማፍራት ለወጣቶች የአመለካከት ለውጥ የሚፈጥሩ  ስልጠናዎች  በፌደራል ደረጃ ታቅደው  በሀገራችን በሁሉም ክልሎች ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡

    በስልጠናው የተሳተፉ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ወቅቱን ጠብቆ መሰጠቱን ገልፀው እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ተከታታይነት ኖራቸው የወጣቱን አመለካከት በመቀየር የሀገራችን ሰላም ለማረጋገጥ ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል ፡፡

    በስልጠናው ከድሬደዋ አስተዳደርና ከሐረሪ ክልል የወጣት አደረጃጀት አመራሮች፣ተፅዕኖ ፈጣሪ አመራሮችና ከከተማና ከገጠር የተወጣቱ የተለያዩ ወጣቶች በአጠቃላይ 400 የሚደርሱ  ወጣቶች ሰልጥነዋል፡፡

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *