የበደልነውን እና ያስከፋነውን ህብረተሰብ ለመካስ ቃላችንን አድሰናል ፡፡ የድሬደዋ ፖሊሶች በጅግጅጋ የመጀመሪያው ዙር የተሀድሶ ስልጠና ተመራቂዎች፡፡

    ግንቦት 7/2011 ጀምሮ ለ1 ወር በጅግጅጋ ከተማ የተሀድሶ ስልጠና የወሰዱ 607 የአስተዳደሩ ፖሊስ አባላት ተመረቁ ፡፡

     

        በምረቃ ስነ -ስርአት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአስተዳደሩ ምክትል ከኒትባና የንግድ ኢንዱሱትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ  ከድር ጆሀር እንደተናገት የወሰዳችሁትን ስልጠና ወደ ተግባር በመለወጥ ባለፉት ጥቂት ወራት በአስተዳደሩ በተከሰተው ውከት የበደላችሁትንና ያስቀየማችውትን ህዝብ ውጤታማ ፖሊሳዊ አገልግሎት በመካስ የህዝቡ እና የሀገር አሊንታኔታችሁን  ማረጋገጥ ይኖርባችዋል ብለዋል፡፡

     ምክትል ከንቲባው ከዚህ ጋር አያይዘው ኃላፊነት ለጣለብን ማህበረሰብ ትልቅ አክብሮት በመስጠት በህገመንግስቱ ስርአት ብቻ ለማገልገል  ከቤሄርተኝነት ፣ከጎሰኝነት አመለካከት ችግር  ወተን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በጋራ እንሰራለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

     የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሙሽን ኮሙሽነር  አቶ አለሙ መርጋ በምርቃ ስነ-ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት  ኮሙሽኑ ከጀመረው የሪፎርም ስራ ውስጥ አንዱና ዋንኛ ተግባር የተቋሙን አባላት በአመለካከት ፣በስነ-ምግባርና በክህሎት እንዲሁም በአካል ብቃትና በአሰራር የተለወጠ ማንነት እንዲኖረው ማስቻል ነው በማለት በቀጣይ እራሱንና አካባቢውን መለወጥ የሚችል ፖሊስ ሆናችው የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ወጥ አቋም ያለው ህዝባዊ ወገኝተኝነትን ያረጋገጠ ለህገ መንግስቱ ዘብ የቆመ  በአገልግሎት አሰጣጣችሁ የህዝብ ታማኝነትን ያተረፈ የፖሊስ ሀይል እንድትሆኑ የታሀድሶ ስልጠና መሰጠቱ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

    በስልጠናው የተሳተፉ የመጀመሪያው ዙር  ሰልጣኞች በሰጡት አስተያየት  በስልጠናው የአመለካከት ፣የክህሎትና የስነ-ምግባር እንዲሁም የአካል ብቃት በመሰጠቱ  እራሳቸውን እንዳደበሩ ገልፀዋል፡፡

    ሰልጣኞች አክለውም  ከቤሄርተኝነትና ከዘረኝነት ፀድተን ህዝቡን በፍታዊነት እና በታማኝነት ለማገልገል  መጀመሪያ የገቡትን  ቃል አድሰው ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ፡፡

    በኩማንደር  ቢኒያም ፍቅሩ በቀረበው የ30 ቀን የስልጠና ሪፖርት የአስተዳደሩ  629 ፖሊስ አባላት የተሃድሶ ስልጠና ለመውሰድ ገብተው 607 አባላት መመረቃቸውንና 22 አባላት  በጤና ችግርና በስነ ምግባር  ችግር አለመመረቃቸውን በቀረበው ሪፖርት ተገልፃል፡፡

    ከስልጠና በተጨማሪ  የክህሎትና የማነቃቂያ ንግግር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በስልጠናው ላይ በመገኘት ጉብኝት ማካሂዳቸውንም በሪፖርቱ ቀርቦል፡፡

    በምርቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛና መካከለኛ  አመራሮች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች የሱማሌ ክልል ተወካዮች ተገኝተዋል ፡፡

    በመጨረሻም ተመራቂ የፖሊስ አባላት የበደልነውን ህብረተሰብ በገባነው ቃል ለማገልገል የገባነውን ቃል አናድሳለን በማለት የቃል መግባት ስነ-ስርዕት አካሄደዋል፡፡

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *