በውጪ ሀገር ቆይታ ግዜያቸው ሀብትና ንብረት ያፈሩ ዜጎቻችንን ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው ኢንቨስት በማድረግ እራሳቸውን፣ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን እንዲጠቅሙ ለማድረግ መንግስት በርካታ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
እንደ ድሬድዋ የዳያስፖራውን ፍሰት ለመጨመርና ልማታዊ ተሳትፎውን ለማሳደግ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም ፖሊሲውን በሚገባ ከመተግበርና የላቀ ውጤት ከማስመዝገብ አንጻር ገና ብዙ መሰራት እንዳለበት ይታመናል፡፡ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ወቅት በአስተዳደራችን ያለውን ምቹ ሁኔታ አጉልቶ በማውጣት በውጪ ሀገራት የሚኖረውን ዜጋ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጥ በማድረግ በሀገር ቤት ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎቱን የማነሳሳት እና ወደ አስተዳደሩ የሚመጣውን ዲያስፖራም ጉዳይ ተቀብለው የሚያስተናግዱ የመንግስት ተቋማት በፍላጎትና በእውቀት ላይ የተመረኮዘ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ በማስቻል እርካታን ለማሳደግ ስልት ቀይሶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
ዲያስፖራ ሲባል ሀገሩን ወዶ አገሬንና ህዝቤን በእውቀቴ አገለግላለሁ የሚል ነው፡፡ በዚህ ረገድ አሁን እየተመዘገበ ላለው ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት በሀገር ውስጥ ካለው ዜጋ ተሳትፎ በተጓዳኝ በውጪ ሀገር የሚኖረው ዲያስፖራም አስተዋፅኦ እጅግ የጎላ መሆኑ ስለታመነበት በውጪ ሀገር ቆይታ ግዜያቸው ሀብትና ንብረት ያፈሩ ዜጎቻችንን ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው ኢንቨስት በማድረግ እራሳቸውን፣ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን እንዲጠቅሙ ለማድረግ መንግስት በርካታ ጥረቶችን በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህም እንቅስቃሴ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፉአድ ሱጌ ገልፀዋል፡፡
የመድረኩ አላማም የዲያስፖራውን ችግር እንዲፈታ እንዲሁም የሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት በህዝቦቿ የጋራ ትብብርና በጎ ፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተ ልማታዊ ተሳትፎ የሚመጣ በተጨማሪም ዲያስፖራውን በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች ያሉ ችግሮችሮች ላይ መፍትሄዎችን በመፈለግ ዲያስፖራው እራሳቸውን፣ አገራቸውንና ህዝባቸውን የሚጠቅሙበትን መንገድ መፍጠር እንደሆነና የዲያስፖራውን በአገር ኢኮኖሚ ከማካተት ዙሪያ ያጋጠሙ ችግሮችን በደንብ ታይተውና ተፈትሸው ለነዚህ ችግሮችም መፍትሔ በመፈለግ የውይይቱ አላማ እንደሆነ አቶ ፉአድ አክለው ገልፀዋል፡፡


