8ኛው የመከላከያ ሰራዊት ቀን በኢፌዴሪ አየር ኃይል የምስራቅ አየር ምድብ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው፡፡

    ‹‹የሀገራችንን ሉዓላዊነት የህዝባችንን ሰላም በፅናት እንጠብቃለን›› በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ባለው በዓል ሰራዊቱ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የልማት ሰራዎቶችን እንዲጎበኝና ግንዛቤ እንዲኖረው መደረጉን የምስራቅ አየር ምድብ እንዶክትሪኒሽን እና የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ እንደገለፁት ኃላፊ ሻምበል ጌታችው ማሞ አስረድተዋል፡፡
    ሰራዊቱ የልማት ሰራዎችን መጎብኘቱ የኔነት ስሜት እንዲኖረው እንዲያስብ በኤፌዴሪ አየር ኃይል የምስራቅ አየር ምድብ ዋና አዛዥ ኮሬኔል አበበ ለገሰ ተናግረዋል፡፡
    ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በመጠበቅና ህዝቡን የማገልገል ተልዕኮውን እንዲወጣ እንደዚህ አይነት ግንዛቤዎች እንዲኖሩት ማድረግ ይበልጥ ጠቃሚ መሆኑን በጉብኝቱ የተሳተፉ የምስራቅ አየር ምድብ አባላት ገልፀዋል፡፡
    በአየር ምድብ 8ኛው የመከላከያ ቀን በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል ፡፡