የድሬዳዋ ፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ድሬዳዋን ፅዱ፣ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግ አላማን ለማሳከት የቋቋመ ተቋም ነው፡፡
እኛም በከተማችን የአረንጓዴ ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ በድሬዳዋ አስተዳደር ፅዳትና ውበት ኤጀንሲ የአረንጓዴ ልማት፤ የመናፈሻ ፓርክና የዘላቂ ማረፊያ የስራ ሂደት ባለቤት የሆኑት አቶ ቢቂላ ታደሠን ያነጋገርን ሲሆን ከአረንጓዴ ልማት ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት በከተማችን በርካታ ቁጥር ያላቸውን የቀን ሰራተኞች በማሳተፍ አመርቂ ስስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ከተማችንን አረንጓዴ የማደረግና የማልማት ስራ የመንግስት ብቻ አለመሆኑን የገለፁት አቶ ቢቂላ ህብረተሰቡ በተለይም ባለሀብቱ የተመረጡ ቦታዎችን በማልማት እግረ መንገዱን ምርትና አገልግሎቶታቸውንም በማስተዋወቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ሁሉም የከተማ ነዋሪ እንዲሁም ባለሀብቶች በመኖሪያ ቤቶቻቸውና በንግድ ቤቶቻቸው አካባቢ ከ20-50 ሜትር ርቀት/ራዲየስ ድረስ እንዲያለሙ በአዋጅ የተደመገገ በመሆኑ ይህንኑ ህብረተሰቡን በማስገንዘብ ተግባራዊ ለማድረግ ይሰራልም ብለዋል፡፡


