በትላንትናው ዕለት ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ/ም ረፋድ 3 ሰዓት ገደማ በቀበሌ 05 በተለምዶ ገንደ ጉራጌ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በተፈጠረ ግጭት ሙራድ ሲራጅ የተባለ የ35 ዓመት ወጣት በደረሰበት ድብደባ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን በአንድ ሌላ ግለሰብ ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ ይገኛል፡፡

    በግጭቱ መኖሪያ ቤቶች በድንጋይ ተደብድበዋል በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡
    ግጭቱን ተከትሎ ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ፖሊስ የአደጋውን መንስዔና ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ምርመራውን በስፋት እያጠናከረ መሆኑን የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና የለውጥ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ አስታውቀዋል፡፡

     

    በቀጣይም ፖሊስ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጥፊዎቹን በመያዘ ለህግ እንደሚያቀርብ ገልጾ በሙራድ ሲራጅ ህይወት ማለፍ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለሟች ቤተሰብና ለቅርብ ወዳጆቹ በአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ስም መፅናናት ተመኝተዋል፡፡