በአስተዳደሩ የክረምት በጎ ፍቃድ በነገው ዕለት እንደሚጀመር የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮምሽነር አቶ ሻኪር አህመድ አሊ ዛሬ ለሚዲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

    ክረምቱን በጥንቃቄ፣በበጎነትና አረንጓዴ አሻራ በማኖር እናሳልፍ የሚል መሪ ቃል ለሁለት ወራት በተለያዩ መርሃ ግብር ከ50 ሺህ በላይ በገጠርም በከተማውም እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡

     

    ከመርሃ ግብሮቹ መካከል የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ በቀጥታ ድጋፍ የሚሹ የአስተዳደራችን ነዋሪዎች የማዓድና የቤት እድሳት እና ኮሮና ቫይረስን ከማህበረሰቡ ለመከላከል የግንዛቤ መስጠት ሥራዎቹ ተጠናክሮ የማስቀጠል ተግባራትን ወጣቶቹ የክረምት ጊዜያቸውን በማሳለፍ እሰከ 40 ሚልዮን ብር የሚገመት ሥራ ለመስራት ተቅዷል ብለዋል ኮሚሽነር ሻክር አህመድ፡፡