ድሬዳዋ ለጅቡቲ ወደብ ቅርብ እንደመሆኗ የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ተባለ

    የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በድሬዳዋ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡

     

    የማህበረሰቡን ለኮረና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያግዝ የግንዘቤ ማስጨበጥ ተግባርም በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ወ/ሮ ለምለም ገልጸዋል ፡፡

    ድሬዳዋ ለጅቡቲ ወደብ ቅርብ እንደመሆኗ ከጅቡቲ ለሚገቡ ዜጎች የለይቶ ማቆያና ህክምና ዋና ማዕከል ሆኖ በማገልገል ላይ ነው ብለዋል፡፡

    በዚሁ መሰረት በደወሌ የማቆያ ጣቢያ የነበረውን መጨናነቅ ለማስቀረት ከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ማዕከሉ ወደ ድሬዳዋ እንዲዘዋወር መደረጉን ገልጸው በማእከሉ ተገቢው አገልግሎት እንዲሰጥና ታካሚዎች በስነ ልቦና ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ተግባራት በቀጣይ የሚከናወኑ መሆናቸውን ወ/ሮ ለምለም ጠቁመዋል፡፡

    በደወሌ ለይቶ ማቆያ ጣቢያ የነበረውን መጨናነቅ ለማስቀረት የሚያስችል ስራ መከናወኑ ታውቋል፡፡