የትራፊክ አደጋን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ዉይይት ተካሄደ
የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የድሬዳዋ ቅ/መስሪያ በድሬ ደዋ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረና እየከፋ የመጣዉን የትራፊክ አደጋ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ የፓናል ዉይይት ተካሄደ፡፡
በዚህ የፓናል ዉይይት ላይ የትራፊክ አደጋ በአስተዳደሩ ያለበትን ሁኔታን ፣ መንስኤዎቹ እና የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚያሳይ ጥናታዊ ፁሁፍ ቀርቦ የዉይይቱ ተሳታፊዎች ሰፊ ዉይይት አካሄደዉበታል፡፡
“ከጳግሜ እስከ ጳግሜ እንደርሳለን“ በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ ወደ ትግበራ መገባቱ ተገለፀ ፡፡
በትራንስፖርት ባለስልጣን የድሬዳዋ ቅ/መስሪያ ቤት ይህን መርሀ ግብር “የትራፊክ አደጋ መከላከል ይመለከተኛል“ በሚል መሪ ቃል መሰረት የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ ወደ ስራ በአስተዳደሩ ከጳግሜ 1 ጀምሮ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጫበጫ እና የቁጥጥር ስራዎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የትራፊክ አደጋን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ዉይይት ተካሄደ ፡፡


