በመጪው የ2013 አዲስ ዓመት በአስተዳደሩ ዘላቂ ሰላምና ጸጥታን በማስፈንና ኮሮና መከላከል ላይ የተወጠኑ ዕቅዶችን ከዳር በማድረስ በሁሉም መልኩ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንሰራለን ብለዋል፡፡
ከንቲባው አህመድ መሀመድ ቡህ መጪውን አዲስ ዓመት በማስመልከት ለነዋሪው ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫቸው የተጠናቀቀው 2012 ዓ.ም በርካታ ውጤቶችና ፈተናዎች በጋራ የተስተናገዱበት እንደነበር አውስተዋል፡፡
አስተዳደሩም ያለፈው የ2012 ዓ.ም መልካም ውጥኖችን አጠናክሮ በማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ አዲስ ዓመት በሁሉም መልኩ ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ላይ ይሰራል ብለዋል፡፡ በተለይም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ፈተና ሆነውብን ያለፉትን የጸጥታና የኮሮና ወረርሺኝ በቀጣይ ከማህበረሰባችን ጋር በጋራ በመሆን መክተን የተሻለና ውጤታማ ስራ ለመስራት ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ የማህበረሰቡ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም ህብረተሰቡም ለህዳሴው ግድብ የሚያደርገውን ርብርብ በማጠናከርና ኮሮናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ተሳታፊ እመንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡


