ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሊክ ልዩ ፅ/ቤት ፣ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የድሬዳዋ እና ጅቡቲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለድሬዳዋ ህዝብ እንዲሁም ለመላው አለም ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያን የ2013 አዲስ አመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዓሉ ስናከብር የተፈናቀሉ ወገኖች በመጎብኘት ማክበር ይኖርብናል በማለት ማህበረሰቡም እነዚህን ወገኖቻችንን መልሶ በማቋቋምና በመርዳት ወደቀድሞ አኗኗራቸው ተመልሰው የደስታቸው ተከፋይ እንድንሆን ማድረግ የጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ከዚህም ጋር በማያያዝ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ለሶስት ሺህ አመት ስለ ሰላም ስታስተምርና ስትሰብክ መኖሯን ጠቁመው አሁንም ለአዲሱ ትውልድ እየሰበከች እንደምትገኝ ገልፀዋል፡፡ ወጣቱንም ስለሰላም በማስተማርና ቤተክርስቲያኗ የሰላም አምባሳደር በመሆን ወጣቱ ለወደፊት አገር ተረካቢ እንዲሆን እየሰራች እንደምትገኝም አክለው ገልፀዋል፡፡
ዓለም አቀፋዊ ቀውስ የሆነው የኮሮና ወረርሽኝ ዙሪያም ህብረተሰቡ ማህበራዊ ርቀትን ጠብቀው ፀሎትን ማድረስ እንዲሁም የህክምና ባለሞያዎች የሚሰጡትን ምክር በመተግበር ከዚህ አስከፊ በሽታ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲጠብቁ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ አሳስበዋል፡፡
በተለያዩ ቤተክርስትያነን በዓሉ አከባበር በስርዓተ ፀሎትና በምስጋና እንዲሁም እግዚአብሔር ጤናችንን እንዲጠበቅ፣ ሰላማንን እንዲያፀና በመመኘት የተጀመሩ እንደ አባይ ያሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ብፁዕ
ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ተመኝተዋል፡፡


