ድሬዳዋ ለጅቡቲ ወደብ ቅርብ እንደመሆኗ የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ተባለ

    የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በድሬዳዋ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡   የማህበረሰቡን ለኮረና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያግዝ የግንዘቤ ማስጨበጥ ተግባርም በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ወ/ሮ ለምለም ገልጸዋል ፡፡ ድሬዳዋ ለጅቡቲ ወደብ ቅርብ እንደመሆኗ ከጅቡቲ ለሚገቡ ዜጎች የለይቶ ማቆያና ህክምና ዋና ማዕከል ሆኖ በማገልገል ላይ…

    Read More

      በአስተዳደሩ የክረምት በጎ ፍቃድ በነገው ዕለት እንደሚጀመር የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮምሽነር አቶ ሻኪር አህመድ አሊ ዛሬ ለሚዲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

      ክረምቱን በጥንቃቄ፣በበጎነትና አረንጓዴ አሻራ በማኖር እናሳልፍ የሚል መሪ ቃል ለሁለት ወራት በተለያዩ መርሃ ግብር ከ50 ሺህ በላይ በገጠርም በከተማውም እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡   ከመርሃ ግብሮቹ መካከል የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ በቀጥታ ድጋፍ የሚሹ የአስተዳደራችን ነዋሪዎች የማዓድና የቤት እድሳት እና ኮሮና ቫይረስን ከማህበረሰቡ ለመከላከል የግንዛቤ መስጠት ሥራዎቹ ተጠናክሮ የማስቀጠል ተግባራትን ወጣቶቹ የክረምት ጊዜያቸውን…

      Read More

        በትላንትናው ዕለት ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ/ም ረፋድ 3 ሰዓት ገደማ በቀበሌ 05 በተለምዶ ገንደ ጉራጌ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በተፈጠረ ግጭት ሙራድ ሲራጅ የተባለ የ35 ዓመት ወጣት በደረሰበት ድብደባ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን በአንድ ሌላ ግለሰብ ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ ይገኛል፡፡

        በግጭቱ መኖሪያ ቤቶች በድንጋይ ተደብድበዋል በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡ ግጭቱን ተከትሎ ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ፖሊስ የአደጋውን መንስዔና ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ምርመራውን በስፋት እያጠናከረ መሆኑን የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና የለውጥ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ አስታውቀዋል፡፡   በቀጣይም ፖሊስ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጥፊዎቹን በመያዘ ለህግ…

        Read More