በምስጋና ዝግጅቱ ላይ ከንቲባ አህመድ ቡህ እና አቶ እዝቅያስ ታፈሰን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸውና በቀድሞው ጊዜ ስመጥር የነበሩ መቶ የሚሆኑ ስፖርተኞችና መምህራን ተገኝተዋል።
የኮረና ወረርሺኝ መከሰቱን ተከትሎ
የቀድሞ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች በነበረው አቶ ተካበ ዘውዴ አነሳሽነት እርስበርስ መደጋገፍን መነሻ ያደረገው በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ማህበር
በድሬዳዋ ለሚገኙ የአረጋውያን ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን በተናጥልም ቀደምት ለሆኑ
ስድስት አረጋውያን ለእያንዳንዳቸው ከስምንት ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።
ዛሬ የአስተዳደሩ ከንቲባ ፅ/ቤት ባደረገው ድጋፍ በራስ ሆቴል በተዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም ላይም በደርግ ዘመነ መንግስት ለ10 አመት ያህል የድሬዳዋ ከንቲባ ሆነው ላገለገሉት ለአቶ አበበ እሸቴ እንዲሁም በቅርቡ በሞት ለተለዩት የቀድሞ የጨርቃ ጨርቅ ተጨዋቾች አቶ ከተማ ቀርሳ እና አቶ ታደሰ አገኘሁ ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።


