ጎዳና የሚወጡ ልጆችን ትኩረት በመስጠት የበኩላችንን ግዴታ መወጣት እንዳለብን ተጠቆመ፡፡

    በተለያዩ ሁኔታዎች ጎዳና የሚወጡ የህብረተሰቡ ክፍሎች በጎዳና ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለማቃለል የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን የሰራተኛና ማህበራዊ እና ሴቶችና ህጻናት ቢሮ በጋራ በመሆን ከpostive action for development (ፖሰቲቭ አክሽን ፎር ድቭሎፕመንት) ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተለያዩ የሙያ ስልጠናዎች ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎች አስመርቋል፡፡
    በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተለይም አይችሉም የሚባሉትን በተለያዩ ችግሮች ህይወታቸውን በጎዳና የሚያሳልፉ ህጻናትና እናቶች እንዲሁም ወጣቶችን ከጎዳና በማንሳት ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ በተለያዩ ስልጠናዎች እንዲሰለጥኑና የራሳቸው ገቢ እንዲኖራቸው የሚደረጉት ጥረቶች ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
    በሌላ በኩል የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ከሪማ አሊ እንደተናገሩት በተለይም ድሬዳዋ ለባህር በር ቅርብ በመሆናችን የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና በተለያዩ ችግሮች የህጻናት ህይወት ጎዳና ላይ ይወድቃል ስለዚህ ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ከፌደራል ሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ዜጎች ከአስከፊው ጎዳና ህይዎት እንዲወጡ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ እንቅስቃሴ ገብተዋል ብለዋል፡፡
    የሰራተኛና ማህበራዊ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሸርማረኬ መሀመድ እንደገለጹት በ4 የተለያዩ ለፕሮጀክቶች ከ6 ሺህ በላይ ህይወታቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎች ታቅፎ በሴፍትኔት ወይም የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገገጥ የቤት ለቤት ድጋፍ የሚደረግላቸው ይገኙበታል ብለዋል፡፡
    በዚህ የምረቃ ፕሮግራም የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ጭውውቶችን በማቅረብ የዕለቱ ተመራቂዎች በእንጨት ሥራ፣በጂብሰን ሥራ እና በቀለም ቀቢነት ስልጠና የወሰዱ ታዳጊዎች ተመረቀዋል፡፡
    በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት አመራር እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በኢትዮ-ጣሊያን መሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተዋል፡፡