በድሬደዋ አስተዳደር በተለያዩ ወቅቶች የህዝቡን የመሰረተ ልማት ፍላጎት ይመልሳሉ የወጣቱን የስራ አጥነት ችግር ይቀርፋሉ ተብለው በመንግስትና የአለም ባንክ ትብብር የተገነቡ የግንባታ ፕሮጀክቶችና የመንግስታዊ ስራውን በማቀላጠፍ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመፍታት አጋዥ የሆኑ ተሸከርካሪዎችና ቁሳቁሶች ግዣቸውና ግንባታቸው ተጠናቀው ለምረቃ በቅተዋል፡፡ በስነስረአቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁኃር በወቅቱ እንደተናገሩት በአስተዳደሩ ባለፉት አመታት በግንባታና ግዠ ላይ የሚስተዋሉ የመዘግየትና ፕሮጀክቶችን ፈጥኖ የመጨረስ ችግር በመቅረፍ እንደሃገርም ሆነ አስተዳደር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የህዝቡን ጥያቄ ፈጥነው ሊፈቱ ሚችሉ የልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በመጨረስ ዘመኑ ቃል የመግባት ሳይሆን ቃልን የመፈፀምና ማህበረሰብን ችግር ፈጥኖ የመፍታት መሆኑን መሳያ ናቸው ብለዋል የለቱን የካፒታል ፕሮጀክቶች ምረቃ፡፡
በቀጣይም ቅድሚያ ሚሹ የማህበረሰብ ችግር ላይምትኩረት ተሰቶ ይሰራልም ብለዋል፡፡
የአስተዳደሩ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ በበኩላቸው በአስተዳደሩ ከግንባታና ግዠ ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ መዘግየቶችን በመፍታት እንዲሁም ተጀምረው ረጅም አመታት ሲፈጁ የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ቀድሞ በማጠናቀቅ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው በአስተዳደሩም በዘንድሮው በጀት አመት ከአዳዲስ ፕሮጀክቶች ይልቅ ለጅምር ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ሰተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
በእለቱም በ2012 በጀት አመት 214ሚሊየን 222ሺ207 ብር ወጭ ተደርገው የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችና ለመንግስታዊ ስራው መቀላጠፍ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች ግዥን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማከናወን በእለቱ ለምረቃ ማብቃታቸውንም ተናግረዋል፡፡
በእለቱ ለምረቃ ከበቁት መካከልም የሁለት አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ማስፋፊያ ግንባታዎች፤የአንድ ጤና ጣቢያ ደረጃ ማሳደግ ፕሮጀክት የገበያ ማእከል ግንባታ እንደሁም የመሬት ልማት ህንፃ ገንባታን ጨምሮ ለተለያዩ አገልግሎት ሚውሉ 58 ከባድና ቀላል ተሸከርካሪዎች እንደሚገኙበትም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
በስነስረአቱ ላይ የተሸከርካሪ ድጋፉን ያገኙ ተቋማትም ድጋፉ ስራን ያቀላጥፋል ያሉብንን ውስንነቶችም ይቀርፋል ብለዋል፡፡
በእለቱከተመረቁትና ለጉብኝት ከበቁት መካከል ሼዶች የመንግስታዊ አገልግሎት መስጫ ህንፃዎች የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችና የተለያየ መጠን ያላቸው ተሸከርካሪዎች ይገኙበታል፡፡


