በድሬደዋ አስተዳደር በ2013 በጀት አመት የመንግስታዊ ስራን ያቀላጥፋሉ የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ይመልሳሉ የተባሉ ከ214ሚሊየን ብር በላይ የወጣባቸው የግንባታና ግዠ ፕሮጀክቶች ለምረቃ በቁ፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር በተለያዩ ወቅቶች የህዝቡን የመሰረተ ልማት ፍላጎት ይመልሳሉ የወጣቱን የስራ አጥነት ችግር ይቀርፋሉ ተብለው በመንግስትና የአለም ባንክ ትብብር የተገነቡ የግንባታ ፕሮጀክቶችና የመንግስታዊ ስራውን በማቀላጠፍ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመፍታት አጋዥ የሆኑ ተሸከርካሪዎችና ቁሳቁሶች ግዣቸውና ግንባታቸው ተጠናቀው ለምረቃ በቅተዋል፡፡ በስነስረአቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁኃር በወቅቱ እንደተናገሩት በአስተዳደሩ ባለፉት…


