በአስተዳደሩ በ2012 በጀት ዓመት ስራቸው የተጠናቀቁ የካፒታል ልማት ፕሮጀክቶች የምረቃ ስነስርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

    በዛሬው እለት ከሚመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው ለተለያዩ የመንግስት ስራ የሚውሉ 40ፒክአኘ መኪናዎች ፣2 የእሳት አደጋ መኪናዎች ፣ 2የውሀ መጓጓዥ ቦቴዎች ፣10 የደረቅ ቆሻሻ መኪኖች 4 የስጋ ማመላለሻ መኪኖች ሲሆኑ መኪኖቹ ከ148ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሆነባቸው ናቸው። በስነስርአቱ በአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቀዋል። በዛሬው እለት የሚመረቁ የግንባታ ስራዎችን በቀጣይ መረጃዎችን እናደርሳለን።