በጁንታው የህወህት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በደረሰው ጥቃት ግዳጅ ላይ ሆነው ለቆሰሉና በምስራቅ እዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ላሉ አባላት የገንደ ሀኖሌ ነዋሪዎች ግምታቸው 40ሺህ ብር የሚገመት የፍየል ሙክት ደግፈዋል ።
በድጋፍ አሰጣጥ ስነስርአቱ ላይ የምስራቅ እዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ሀላፊ ኮርኔል ብርሀኑ ዘመዴ ህዝቡ ለመከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ ህዝባዊ ወገንተኛነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል ።ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል ።
ከህዝቡ የተሰበሰበውን ድጋፍ ያበረከቱት ተወካዮች መከላከያ ሰራዊት ከተለያዩ የብሔርብሔረሰቦች የተወጣጣ እንዲሁም ካለምንም ማዳላት የሚሰራ እንደመሆኑ በማንኛውም ሰአት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ።


