የድሬደዋ አስተዳደር ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን አገራዊ ጥሪ ተቀብለው ሀብት፤ጉልበትና እውቀት በመለገስ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሀገር አለኝታዎችና ዋልታዎች በድሬዳዋ ራስ ሆቴል የምስጋናና የዕውቅና ስነስርዓት አካሄዶል።
በስነ ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀር እንደተናገሩት በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት የጁንታው የህውሀት ቡድን በፈፀመው ክህደት የሕግ ማስከበር ስራ የህዝብ አለኝታ መሆናቸውን ላሳዪት የመከላከያ ሰራዊቶች በአይነት እና በገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ግለሰቦችና ተቋማት በአስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ በእንዲ እንዳለም ለመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ድጋፍ እንዲደረግ የድርሻቸውን ለተወጡ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን የቸሩት ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጆሀር ለሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ በአስተዳደሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የድሬደዋ አስተዳደር ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ በበኩላቸው በአስተዳደሩ በገጠርና በከተማ በአይነትና በገንዘብ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች በፓርቲው ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በምስጋናና በእውቅና መረሀ ግብሩ ላይ የሐይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዋችና የአፍረን ቀሎ አባ ገዳ የምርቃት ስነስርአት ያካሄደዋል።
በመጨረሻም ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን አገራዊ ጥሪ ተቀብለው ሀብት፤ጉልበትና እውቀት በመለገስ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሀገር አለኝታዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።


