ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ድገፍ ላደረጉ የምስጋናና የዕውቅና ሰነስርአት ተካሄደ።
የድሬደዋ አስተዳደር ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን አገራዊ ጥሪ ተቀብለው ሀብት፤ጉልበትና እውቀት በመለገስ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሀገር አለኝታዎችና ዋልታዎች በድሬዳዋ ራስ ሆቴል የምስጋናና የዕውቅና ስነስርዓት አካሄዶል። በስነ ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀር እንደተናገሩት በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት የጁንታው የህውሀት ቡድን በፈፀመው ክህደት የሕግ ማስከበር ስራ…


