በድሬዳዋ ሴቭ ዘ ቺልድረን 1.5 ሚሊየን ወጪ የተገነባው የህጻናት ህገ ወጥ ዝውውርን ለመቀነስና ለመቆጣጠር እንዲያድችል የተገነባ የ12 ህጻናት ማቆያ ምርቃት ተካሄደ።
ከፍተኛ የህጻናት ዝውውርን ለመቀነስና ለመቆጣጠር ታስቦ የተገነባው ድርጅቱ የበኩሉን ለመወጣት በቅንጅት በመስራት ወደ ቤተሰባቸው ለማቀላቀል በመንገድ ትራንስፖርት ግቢ ትብብር ማዕከሉ ተገንብቷል።
በማዕከሉ 12 የወንዶችና የሴቶች ህጻናት ማቆያ፣ መምከሪያ፣ መረጃ ክፍል (council room) እና የተሟላ መጸዳጃ ያለው ሲሆን በቀጣይ ማዕከሉን የአስተዳደሩ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ በባለቤትነት እንደሚመራው ታውቋል።
ድሬዳዋ ለህገወጥ ፍልሰት ተጋላጭ ኮሪደር በመሆኑ የህጻናት መብትና ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር እንዲሁም ከህጻናት ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን ለማስቀረት ከፍተኛ አስተዋጽአ እንደሚኖረው በሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ተገልጿል።
ለህጻናት ማቆያ ምቹ ቦታ መኖር ስለሚገባ በሴቭ ዘ ቺልድረን ለተደረገው ድጋፍና ትብብር ላደረጉ ለመንገድ ትራንስፖርትና ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና አቅርበው በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም ለስኬቱ ትብብር ላደረጉ ተቋማት የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።


