ኑ ተማሪዎች ላፍታም ሳንዘናጋ ሁላችንም ወደ ትምህርት ቤታችን እንመለስ!!!

    የነገ የሀገር ተስፋ የሆናችሁ ተማሪዎች ይህችን መተኪያ የሌላትን ሀገር ካላት ራዕይ ጭምር የምትረከቡ እናንተ ናችሁ፡፡ ወላጆቻችሁ እና ሀገራችሁ ከእናንተ ብዙ ይጠብቃሉ፡፡ ከእናንተ የሚፈለገውን ሁሉ መውጣት እንድትችሉ ትምህርት የማይተካ ቁልፍ ሚና አለው፡፡ ትምህርት ለሀገር ዕድገት ቁልፍ ነውና፡፡
    ስለሆነም በኮቪድ-19 ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በአስተዳደራችን በሚቀጥለው ሳምንት ሙሉ በሙሉ ይጀምራል፡፡ ለአፍታም ሳንዘናጋ ሁላችንም ወደ ትምህርት ቤታችን እንመለስ፡፡ የራሱን ብሩህ ተስፋ እና ራዕይ ማሳካት የሚፈልግ ማንኛውም ተማሪ ከትምህርት ቤት መቅረት የለበትም፡፡ ለኮቪድ-19 መፍትሄው ፍርሀት ሳይሆነ ተገቢው ጥንቃቄ ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻችሁን ተገቢውን የኮቪድ-19 ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ወደ ት/ቤት ይውሰዷቸው፡፡
    ይህ አስቸኳይ እና ብርቱ ጉዳይ ለሁሉም ተማሪ እንዲደርስ ሁሉም አካላት በተቀናጀ መልኩ በመቀስቀስ የድርሻውን ይወጣ፡፡ ምዝገባው ከሰኞ ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ይጀመራል፡፡
    ኑ ተማሪዎች ላፍታም ሳንዘናጋ ሁላችንም ወደ ትምህርት ቤታችን እንመለስ!!!
    የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር
    ታህሳስ 16/ 2013 ዓ/ም