የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የደንበኞች ፎረም መድረክ አካሄደዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት አሁን ካለበት ደረጃ በተሻለ በልኩ ለማሳደግ እንዲችል እስከ አሁን ያለውን ልምድ እና በቀጣይ የሚገኘውን ልምድ በመቀመር የመረጃ መለዋወጥ ስርዓቱን በተጠናከረ መልኩ በተቋም ደረጃ የደንበኞችን አገልግሎት አሰጣጥ መሳለጥ እንቅፋት የሆኑ አሰራሮችን ለባለስልጣኑ በመጠቆም እንዲወገዱ የሚያስችል ተግባራት እንደሚቀጥሉ ተገልጸዋል፡፡
ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኃላፊ አቶ መሀመድ ሙሳ የደንበኞች ፎረም የተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥና የእቅድ አፈጻጸሙን በጋራ ስለሚገመግሙ የባለስልጣኑን ሠራተኞች የስራ ትጋትና የአገልግሎት አሰጣጥን እንደሚያሻስል ገልጸዋል፡፡
የከተማ ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱጀዋድ መሀመድ በበኩላቸው የአስተዳደሩ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ይህንን የደንበኞች ፎረም በማዘጋጀት የነዋሪው አስተያየትና ቅሬታ ለመስማት እና ተገቢውን መልስ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡
የደንበኞች ፎረሙ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊዎችና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከከተማው ቀበሌ የተውጣጡ ነዋሪዎች ታዳሚ የሆኑበት መድረክ በውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የተሰሩ ሥራዎችና የ10፣5 እዲሁም የዚህ ዓመት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እቅድ በገለጻ መልክ የባለስልጣኑ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሙሳ አቅርቦ ተወያይተዋል፡፡


