ኑ ተማሪዎች ላፍታም ሳንዘናጋ ሁላችንም ወደ ትምህርት ቤታችን እንመለስ!!!
የነገ የሀገር ተስፋ የሆናችሁ ተማሪዎች ይህችን መተኪያ የሌላትን ሀገር ካላት ራዕይ ጭምር የምትረከቡ እናንተ ናችሁ፡፡ ወላጆቻችሁ እና ሀገራችሁ ከእናንተ ብዙ ይጠብቃሉ፡፡ ከእናንተ የሚፈለገውን ሁሉ መውጣት እንድትችሉ ትምህርት የማይተካ ቁልፍ ሚና አለው፡፡ ትምህርት ለሀገር ዕድገት ቁልፍ ነውና፡፡ ስለሆነም በኮቪድ-19 ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በአስተዳደራችን በሚቀጥለው ሳምንት ሙሉ በሙሉ ይጀምራል፡፡ ለአፍታም ሳንዘናጋ ሁላችንም ወደ ትምህርት ቤታችን እንመለስ፡፡…


