በድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ከ160 በላይ ለሆኑ ለደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች ስልጠና ሰተዋል። ከ14/04/2013 ዓም እስከ 16/04/2013 ዓም ድረስ ለደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች ::

    ለሆቴል፣ግሮሰሪ፣ለልኳንዳቤቶች፣ህንፃ መሳሪያ፣ ስፔር ፓርት እና ሌሎች ዘርፍ ላይ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠ ሲሆን ከሂሳብ ሰነድ አያያዝ እስከ ሂሳብ መግለጫ ያለውን ያጠቃለለ ነው። ዘርፉ በከፍተኛ ሁኔታ ግብይት ስለሚካሄድበት በዘርፉ ያለውን በደረሰኝ ያለመገበያየት ችግርንም ለመቅረፍ የሚረዳ መሆኑ ይታወቃል። በስልጠናዉ ላይ የግብር አንባሳደሮቻችን ስለ ግብር መክፈል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።