6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን ሃሳብ ቀረበ::

    በተያዘው ዓመት የሚካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን ሀሳብ ቀረበ።
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።