በምክክር መድረኩ ላይ የመክፈቺያ ንግግር ያደረጉት የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን እንደገለፁት መድረኩን ያስፈለገበትን ምክንያት ሲገልፁ በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሰራሪን በማጠናከር ከመሬት ጋር ተያይዞ ህጋዊ አካሄድን የተከተለ ቀልጣፋ፤ፍትሃዊ፤ዘመናዊ አገልግሎት ለህዝቡ በመስጠት ከመሬት ጋር የተያያዘዉን የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ የሊዝ አዋጅ ምንነትና በአዋጁ የተቀመጡ ግዴታዎች ፣የከተማ ፕላን አጠቃቀም እና በከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ እንዲሁም የኤጀንሲው ተልዕኮና አላማ ዙሪያ ሰነዶች ቀርበዉ ዉይይት ተካሄዶባቸዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዉበታል፡፡


