ከበአሉ ጋር ተያይዞ መግለጫ የሰጡት የኮሚሽኑ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ኢ/ር አንተነህ ረፌራ እንዳስታወቁት በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ለሁሉም ፈፃሚ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋዥ ተቋማት ቀደም ባሉት ቀናት የበአሉን አከባበር የተመለከተ የፀጥታ እቅድ ወቶ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር ገልፀው አሁን ላይ በአሉ ያለምንም የፀጥታ ችግርና የወንጀል ተግባር በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል በስውርና በግልፅ የሰው ኃይል በመመደብ ወደ ስራ መገባቱን ዳሪክተሩ ተናግረዋል::
ኢ/ር አንተነህ አክለውም ከበአሉ ጋር ተያይዞ ወደ ከተማው የሚመጡ እንግዶች ራሳቸውን ከተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መጠበቅ እንዳለባቸው ገልፀው የተለዩ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ወድያውኑ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠ ይኖርባቸዋል ብለዋል::
ከትራፊክ እንቅስቃሴ ግልር ተያይዞ እንዲሁ መግለጫ የሰጡት የትራፊክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት ዳሬክተር የሆኑት ኢ/ር ይሄነው ሽፈራው በበኩላቸው ከበአለ ንግሱ ጋር ተያይዞ ብዛት ያላቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ከተማ የሚገቡ በመሆኑ ይህንኑ ተከትሎ የመንገድ ላይ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት እና የተሳለጠ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ የትራፊክ ፖሊስ አባለት እና አመራሮች ከወትሮ በተለየ መልኩ ዝግጁ በማድረግ ወደ ስራ መግባታቸውን ዳሪክተሩ ገልፀዋል ፡፡
ዳሪክተሩ አያይዘውም ሊደርሱ የሚችሉ የትራፊክ አደጋዎች ለመከላከል መላ አሽከርካሪዎች በትእግስት የመንገድ አጠቃቀም ህግና ስርአትን በማክበር ከአደጋ ተጠብቀው ሊያሽከረክሩ ይገባል ብለዋል::
ሀላዊዎቹ በመጨረሻም በመልክታቸው ለበአሉ ሰላማዊነት ሁሌም ከፖሊስ ጋር ተባብሮ የሚሰራው መላዊ የአስተዳደሩ ነዋሪ አሁንም በቅንጅትና በትብብር ይበልጥ አብሮ እንዲሰራ እንዲሁም ህዝበ ምእመኑም ከኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆን በተገቢው ሁኔታ የጥንቃቄ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::
ምንጭ -ድሬ ፖሊስ


