ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ በተመረጡ ቦታዎች ተካሄደ።

    15ኛው ሳምንት የጽዳት ዘመቻ በአስተዳደሩ ቀበሌ 02 በተመረጡ ሶስት ቦታዎች ማለትም ቡድን 1. በክቡር ከንቲባው የሚመራው ከሰኢዶ ፎቅ እስከ አዲሱ መነሃሪያ ቡድን 2. በክቡር ም/ ከንቲባው የሚመራው ከሰኢዶ ፎቅ በአጠና ተራ እስከ ጎሮ እንዲሁም ቡድን 3 (ፖሊስ ኮሚሽን) በኮሚሽነሩ የሚመራ ከሰኢዶ ፎቅ እስከ ኢንዱስትሪየጽዳት ዘመቻ ፕሮግራሙ ተካሂዷል።
    በዘመቻው የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የሴክተር መ/ቤት አመራሮች፣ የቀበሌ 02 አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የአከባቢው ህበረተሰብ ተሳትፈዋል፡፡