“ከተማና ፊት ባለቤቱ ነው የሚያጸዳው”

    “ከተማና ፊት ባለቤቱ ነው የሚያጸዳው”
    6በ ሚልየን ብር የተገዙ የጽዳት እቃዎች በከተማችን ለሚሰሩ 16 የቤት ለቤት ደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብ ላይ የተሰማሩ ማህበራት ድጋፍ ተሰጠ፡፡
    የከተtማችን ህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና የከተማው ስፋት እያደገ በመምጣቱ የከተማው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥራ በተፈለገው ሁኔታና ፍጥነት ለማስወገድ አዳጋች በሆነበት በአሁን ጊዜ እንዲህ ያሉ ድጋፎች ለማህበራቱ ትልቅ መነሳሳት እንደሆነ አንዳንድ የማሀበራቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
    በድጋፍ መስጠት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙትና ለማህበራቱ ድጋፉን ያስረከቡት የድሬዳዋ ከተማ ጽዳትና ውበት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ጣሂር ሮብሌ እንደተናገሩት ይህ ድጋፍ ማህበራቱ በጠየቁት መሰረት የተፈጸመ ነው ካሉ በኋላ እንደ ከተማው በአሁን ላይ ያሉ የቤት ለቤት ደረቅ ቆሻሻ በማስወገድ ላይ የተሰማሩ ማህበራት በቂ ባለመሆናቸው በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ያጠናነው ጥናት በቅርቡ ሥራ ላይ ይውላል ብለዋል፡፡
    አያይዞም አቶ ጣሂር ሮብሌ አሁን ያሉትን 16 ማህበራት ወደ 30 ማህበራት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ያሉት አሁን በ9ኙ የከተማ ቀበሌ የሚቀሳቀሱ ማህበራት የእጅ ጋሪ፣ ባለሁለት ጎማ የሚገፋ ጋሪ እንዲሁም ሙሉ የሴፍቲ ልብስ፣ ጫማ፣ መነፅር እና ጓንት ኤጀንሲው ያደረጋል ብለዋል፡፡
    በዚህ ሥራ የተሰማሩ ማህበራት የሚያነሱትን የደሞዝ መስተካከል ጥያቄም በቅርብ ጊዜ የአስተዳደሩ ካቢኔ ስብሰባ ላይ መልስ እንደሚጠባበቁ ተናግሮ አሁን ድሬዳዋን የቀድሞ የገነነ ስሟን ለመመለስ የሁሉም ሰው ድጋፍና ርብርብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
    ድጋፍ የተደረገላቸው ማህበራትም የተረከቡትን እቃዎች በተገቢው ሁኔታ እንደሚጠቀሙና ከቤት ለቤት የሚወጡ ቆሻሻም በተቻላቸው ፍጥነት በማንሳት ለከተማው ዉበት የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደረጉ ተናግረዋል፡፡