#እኛ_እያለን_ኢትዮጵያ_አትፈርስም!!

    #ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!
    በድሬዳዋ አስተዳደር የቀበሌ 04 ጽ/ቤትና የገንደ ቆሬ ፖሊስ ጣቢያ በጥምረት ባስተባበሩት የድጋፍ አሰባሰብ በገንዘብና በዓይነት ጠቅላላ ግምቱ ከአንድ ሚሊየን ብር($1,000,000.00) በላይ የሆነ ድጋፍ ማሰባሰብ ተችሏል።
    ድጋፉን ያደረጉት በቀበሌ 04 ክልል ውስጥ የሚገኙ አስር(10) የመረዳጃ ዕድሮች ሲሆኑ ድጋፉም የተደረገው በገንዘብና በዓይነት ሲሆን:-
    #በጥሬ ገንዘብ $385,600.00(ሶስት መቶ ያሰማን አምስት ሺህ ስድስት መቶ ብር)
    #20 ኩንታል በሶ
    #5 ኩንታል ዳቦ ቆሎ
    #50 ማዳበሪያ አልባሳት ሲሆን፤
    #አንዲት እናት 4 ግራም ወርቅ የጣት ቀለበታቸውን ለግሰዋል።
    በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር፣ ምክትል ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የፍትህና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መገራ፣ የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ ደረጃ ፀጋዬ፣ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የቀበሌ 04 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀምዲ መሀመድ፣ የገንደ ቆሬ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኢንስፔክተር አባድር ኢብራሂም፣ የቀበሌ 04 አመራሮችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
    #በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር ባስተላለፉት መልዕክት የዚህ አይነቱ ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ገልጸው ድጋፉን ላበረከቱት የቀበሌ 04 የመረዳጃ እድሮችና ድጋፉን ላስተባበሩት ለቀበሌ 04 ጽ/ቤትና ለገንደ ቆሬ ፖሊስ ጣቢያ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ሌሎች የከተማችን ነዋሪዎችና ማህበራትም የቀበሌ 04 ነዋሪዎችን ዓርአያ እንደሚከተሉ እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል።