ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ አገር ቤት በሚል ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ የዳያስፖራ አባላት የድሬደዋ አስተዳደር አብይ ኮሚቴ ያዋቀረ ሲሆን ይህንን እንቅስቃሴ በተጠናከረ መልኩ ለመወጣት ንዑስ ኮሚቴም አዋቅሮ በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአስተዳደራችን ተወላጅ የዲያስፖራ ማህበረሰብ እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለማስተናገድ ይመች ዘንድ ወደ አስተዳደራችን የሚመጡትን ኢትዮጵያውያን ፤ ትውልደ ኢትዮጵዮውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች አስፈላጊውን የማስተባበር ስራዎችን ለማከናወን መረጃ ለማሰባሰብ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አድራሻ መጠቀም ይችላሉ ፡-
    የስልክ ቁጥር፡-
    0254 11-06-63
    0915440957
    00928191363 እና 0977853708
    እንደዚሁም የዲያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት በድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ህንጻ ላይ 1ኛው ፎቅ ላይ በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
    ማሳሰቢያ፡-የተሟላ ክትትልና ድጋፍ ለማግኘት ከላይ በተጠቀሱት የስልክ መስመሮች እና አድርሻዎች በአካልም ሆነ ስልክ በመደወል ብቻ መመዝገብ ይችላሉ::