የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ከኃላፊነታቸው በክብር ሸኘ

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ከኃላፊነታቸው በክብር በመሸኘት አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህ እና የአሰራር ስርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው ማጠቃለያ ስብሰባው አቶ ደመቀ መኮንንን በሙሉ ድምፅ በክብር ሸኝቷል።

በምትካቸውም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *