ከጥር 13 እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ማጠቃለያ አቶ ተመስገን ጥሩነህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡ የድሬዴዋ አስተዳደርም አቶ ተመስገን ጥላሁን በቀጣይ የስራ ዘመንናቸው መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ተመኝቷል።
የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህንና የአሰራር ሥርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው የማጠቃለያ ስብሰባ በሙሉ ድምፅ አቶ ደመቀ መኮንን በክብር ሸኝቷል። አቶ ደመቀ መኮንን በነበራቸው የስራ ቆይታ ባሳዩት የስራ ታታሪነት የድሬዳዋ አስተዳደር አክብሮቱን ገልፃል።


