ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተውጣጡ የድሬዳዋ አስተዳደር ልጆች ፣ ወዳጆች እንዲሁም ከፈረንሳይ ፣ ከጅቡቲ፣ ከኒጀር፣ ከማሊ፣ እንዲሁም ከዩኤስኤን ጨምሮ ከሌሎች የዓለም ሀገራትም የመጡ የዲያሎግ ሂዩማኒቲ አባላት እና ተሳታፊዎች ለተከታታይ ቀናት በድሬደዋ ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለት የፕሮግራሙ በመዝጊያ የምሳ ግብዣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በቤተመንግስት ተደርጎላቸዋል።
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመገኘት ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ለተከታታይ ቀናት በመስተዳደራችን የተሳካ ቆይታን በማድረጋችሁም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡ በቀጣይም የድሬደዋ አንባሳደሮች በመሆን ትስስሩ መጠናከር በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በምሳ ግብዣው የድሬደዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር፣ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ፈቲያ አደን እንዲሁም የድሬደዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ ኢብራሂም ዩስፍን ጨምሮ በመስተደዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ ያገኘናቸው ተሳታፊ እንግዶችም በድሬደዋ መስተዳደር የተደረገላቸው አቀባበልና መስተንግዶ ከጠበቁት በላይ እንደሆነና ከተማዋ የፍቅር ሀገር መሆኗን ከቃላት በላይ በተግባር ያየንበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ከከተማዋ ጋር ያላቸው ግኝኙነት ተተናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡


