የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ7ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 386 ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 338 በቅድመ ምረቃ፣ 29 በድህረ ምረቃ ትምህርታቸው የተከታተሉ ናቸው።
በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባ አደም ለተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በተለይም ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩኒቨርስቲው ለህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በመስጠት ባጠቃላይ 98 ፐርሰንት ተማሪዎች በማለፋቸው እንኳን ደስ አለን ብለዋል፡፡
በዛሬው እለትም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ተመርቆ ስራ በጀመረበት ቀን በመመረቃችሁ ደስታውን እጥፍ ድርብ ያድርገዋል ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ በትምህርት ቆይታችሁ ያሳያችሁትን ጥንካሬ በስራው አለም መድገም ይገባቹሀል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የኢፌድሪ የጤና ሚኒስትር ዴዔታ የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በበኩላቸው የተመራቂ ተማሪዎች ደስታ ተካፋይ በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልፀው፤ ሀገራችን የብልፅግና ጉዞ ላይ በመሆኗ ይህንን ለማገዝ እናንተም በተማራችሁበት መስክ የራሳችሁን አሻራ ማኖር ይገባቹሀል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በስራ ምክንያትም በምትመደቡበት አካባቢም በጥንካሬ፤ የሙያ ስነምግባርን በጠበቀ መለልኩ እንዲሁም ለታካሚዎች በርህራሄና በእንብካቤ አገልግሎት መስጠት እንደሚስፈልግ ሚኒስተር ደኤታው አንስተው ለተመራቂ ተማሪዎችም መልካ የስራ ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
ተመራቂ ተማሪዎቹ በበኩላች ብዙ ውጣ ውረድን አልፈው ለዛሬ ቀን በመድረሳቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው በቀጣይ በገቡት ቃልኪዳን መሰረት ህዝባቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


